Strong Health Financing for Sustainable Health Development

ጠንካራ የጤና ፍይናንስ ለዘላቂ የጤና ልማት

Message from H.E. Dr. Lia Taddesse for ARM Participants

Dear participants of the 25th Annual Health Sector Review Meeting

As you know, as part of our alignment and harmonization process and based on the health sector’s “One Plan, One Budget, One Report” principles, every year, all key stakeholders of the health sector convene at this time of the year to review the performance of the past fiscal year and agree on major priorities of the current fiscal year. Accordingly, the Ministry of Health, in cooperation with the Addis Ababa City Administration Health Bureau and partner organizations, has organized the 25th Annual Health Sector Review Meeting (ARM) in the beautiful city of Addis Ababa from November 1-3, 2023.  I am happy to announce that this year’s ARM will be conducted under the theme ‘Strong Health Financing for Sustainable Health Development’ which I believe is a relevant and timely topic to focus the discuss on during the two days and give our utmost attention to during this fiscal year and beyond.

This ARM is peculiar that it is held while we are transitioning from the end of the HSTP II to the new three years strategic plan of the health Sector, the Health Sector Medium-Term Development and Investment (2023/24-2025/26).

The ARM is expected to be attended both in person and also virtually to maximize the reach of this grand forum of the health sector. Members of the House of Peoples Representatives, Federal and Regional officials, representatives of development partners, representative of civic and professional associations, the private health sector and academia and other guests from various sectors are expected to participate in the forum.

As usual, the field visit program will be conducted on the 1st of November to selected health facilities and community levels to draw lessons and best practices on selected priority thematic areas of the health sector. The main conference will be opened on November 2, 2023 and various events will be held on the opening and the following day. Among the key events and agenda items are the EFY 2015 performance report of the health sector, highlights of the EFY 2016 and the Health Sector Medium-Term Development and Investment (2023/24-2025/26) plans, presentation of award for distinguished services, mini-exhibition and group discussion and reflections on selected thematic areas relevant to health sector.  Finally, signing of agreement between MOH and RHBs on the core plan of EFY 2016, issuance of joint statement of participants of the ARM and selection of the venue for the next ARM will be held.

As much efforts as possible have been exerted to make the event as inclusive and participatory.

I want to seize this opportunity to respectfully request the invited guests and all participants of the ARM to make an active participation and constructive contributions during the ARM and to implement the key action items emanating from the ARM events It is my heartfelt belief that we will have vibrant and fruitful discussions.

Finally, on behalf of myself and the Ministry, I would like to express my sincere gratitude to the leadership and staff of Ministry of Health and Addis Ababa City Administration Health Bureau, as well as all our partners, for their great contribution to realize this event. I would like to respectfully request all parties to continue their hard work and efforts till the end of the event.

I am looking forward to seeing the invited participants in Addis Ababa, the political capital of Africa and the seat of major international organizations.!

Lia Tadesse, MD, MHA

Minster, Ministry of Health

የክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ መልዕክት

የተከበራችሁ የ25ኛው ዓመታዊ የጤናው ዘርፍ ጉባኤ ተሳታፊዎች

እንደሚታወቀው “አንድ  ዕቅድ፤ አንድ በጀት፣ አንድ ሪፖርት” በሚለው መርሃችን መሠረትየጤናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት በየአመቱ በዚህ ወቅት ባለፈው አመት በጋራ አቅደን የፈፀምናቸውን ቆም ብለን ለመገምገምና በዘንድሮው የበጀት አመት ለመፈፀም ያቀድናቸውን ስራዎች በጋራ ተወያይተን የጋራ ግንዛቤ ለመያዝ ይገናኛሉ፡፡ በዚህም መሠረት  የጤና ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የ25ኛውን አመታዊ የጤና ጉባኤ በውቢቷ አዲስ አበባ ከተማ ከጥቅምት 21-23 ቀን 2016 ዓ.ም ያካሄዳል፡፡

የዚህ ዓመት ጉባኤ የሚከበረው ‘ጠንካራ የጤና ፋይናንስ ለዘቂ የጤና ልማት’ በሚል መሪ ቃል መሆኑን  በደስታ እየገለጽኩ መሪ ቃሉ አግባብነት ያለውና ወቅታዊ በመሆኑ የሁለቱ ቀናት ውይይት ማጠንጠኛ ብሎም በበጀት አመቱና ከዚያም ባሻገር ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ እንደሚሆን ሙሉ እምነቴ ነው፡፡

የዘንድሮውን ጉባኤ የተለየ የሚያደርገው የ2ኛው የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን እቅድ አገባደን ወደ ቀጣይ የሶስት አመታት የጤናው ሴክተር የመካከለኛ ጊዜ የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ እየተሽጋገርን ባለንበት ወቅት መከናወኑ ነው፡፡  

በዚህ ጉባኤ ላይ በአካል ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና ተሳታፊዎች የሚታደሙ ሲሆን ጉባኤውንም በመረጃ መረብ አማካኝነት ተሳታፊዎች መከታተል እንዲችሉ ዝግጅት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ የጤና ጉባኤ ላይም የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች፣ የአጋር ድርጅቶች ፣ የሲቪክና የሙያ ማህበራት፣ የግሉ ዘርፍና የከፍተኝ ትምህርት ተቋማት ተወካዮች እንዲሁም ከተለያዩ  ዘርፎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይሳተፋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

እንደተለመደው በዚህም አመት ጉባኤው ከመከፈቱ በፊት የመስክ ጉብኝት መርሃ ግብር ከአንድ ቀን በፊት ጥቅምት 21 ላይ ይካሄዳል። በዚህም መሠረት በተለያዩ ቡድኖች በመከፋፍል የጤና ተቋማትን እና የማህበረሰባችን ክፍሎች ውስጥ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ያሉበትን ሁኔታና ተሞክሮዎች ይቃኛሉ፡፡ ዋናው ጉባኤ የሚከፈተው ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሆን በመክፈቻው እለትና በማግስቱ በወጣው ፕሮግራም መሠረት የተለያዩ ዝግጅቶች ይካሄዳሉ፡፡ ከዋና ዋና ፕሮግራሞች ውስጥም የጤናው ሴክተር የ2015 ዓ.ም የአፈፃፀም ሪፖርት፤ የ2016 ዓም እና የቀጣይ የሶስት አመታት የጤናው ሴክተር እቅዶች ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡

በተጨማሪም በጤናው ዘርፍ የላቀ አገልግሎት ላበረክቱ ግለሰቦች ሽልማት ማበርከት፤ ኤግዚቢሽን፤ በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ የቡድን ውይይትና ሪፖርት ማድረግ ይከናወናሉ፡፡ ፡ በመጨረሻም  በጤና ሚኒስቴርና በክልል ጤና ቢሮዎች መካከል የ2016 በጀት አመት አንኳር እቅድ ስምምነት የፊርም ስነ ስርዓት፤ የጉባኤው ተሳታፊዎች የጋራ የአቋም መግለጫና የቀጣይ አመት ጉባኤ የሚካሄድበትን ክልል መረጣ ይካሄዳል፡፡

ዝግጅቱም በተቻለ መጠን አሳታፊና ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያካተተ እንዲሆን ጥረት መደረጉን እየገልጽኩ

በዚህ አጋጣሚ ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶችና የጉባኤው ተሳታፊዎች በተለዩና ውይይት በሚደረግበቸው አጀንዳዎች ላይ ግልፅ  ውይይት በማድረግ የቀጣይ እቅዳችንና አቅጣጫችን ላይ ገንቢ አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡

በመጨረሻም ይህ የጤና ጉባኤ ዝግጅቱ የተሳካ እንዲሆን የጤና ሚኒስቴርና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች እንዲሁም አጋር ድርጅቶቻችን ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ሲሆን  ለዚህም በራሴና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስም ከፍተኛ ምስጋና ማቅረብ እወዳለሁ፡፡ ዝግጅቱ ተጠናቆ እንግዶቻችን እስክንሸኝ ድረስ ይህ ትጋትና ጥረታችሁ እንዳይለየን በአክብሮት ለመጠየቅ እወዳለሁ፡፡

 

በአካል የተጋበዛቹትን ተሳታፊዎችን በውቢቷ፤ የአፍሪካ መዲና፤ የዓለም አቀፍ ተቋማት መቀመጫ እንዲሁም የቱሪስት መስህብ እየሆነች በመጣችው አዲስ አበባ ላይ ለማየት ጉጉቴ የላቀ ነው፡፡

ዶ/ር ሊያ ታደሠ

የጤና ሚኒስትር